=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ንባብ በሂወታችን ውስጥ ትልቅ ቦታ ሊኖረው የሚገባ መሠረታዊ ክህሎት ነው። በተሰማራንበት ነገር ሁሉ ስኬታማ ለመሆን ፣ በእምነታችን ጠንካራ ለመሆን ፣ እምነታችነን ሙሉ ለማድረግ እንዲሁም ደስተኛና የተረጋጋ ሂወት ለመምራት እራሳችነን በእውቀትና በጥበብ ልንክን ይገባል።
ይህን ለማድረግ ደግሞ የንባብ ክህሎታችን መግራት ይጠበቅብናል። ወጣቶች አብዛሃኛውን ጊዜ የምናሳልፈው በትምህርት በመሆኑ በትምህርታችን ጐበዝ ለመሆንና በቂና ተፈላጊውን እውቀት ይዘን ለመውጣት የንባብ ክህሎታችንን ከወዲሁ ልናነሻሽል ይገባል።
1) የንባብ ዘዴ
2) የአትኩሮት ንባብ
3) መዝገበ ቃላት
በተለያዩ ሁኔታዎች የምንጠቀማቸው ሶስት የንባብ ዘዴዎች አሉ። እነሱም:-
1) የቅኝት/የአሰሳ ንባብ
ከአንድ ፅሁፍ ውስጥ የምንፈልገውን ነገር ብቻ ለይተን ለማውጣት የምንገለገለው የንባብ አይነት ነው።
2) ግርፍ ንባብ
የፅሁፉን ፍሬ(ዝርዝር) ነገሮች ለማግኘት የምንጠቀመው የንባብ ዘዴ ነው።
3) የዝግታ ንባብ
ሙሉ ፅሁፉን በጥልቅ ለመረዳት የምንጠቀመው የንባብ ዘዴ ነው።
የቅኝት ንባብ ማለት አንድ የምንፈልገው ነገር ካለ ያን ለማግኘት ስንል አይናችነን ከፅሁፉ ላይ በማድረግ ፅሁፉን በፍጥነት ማንበብ ነው። ይህን የንባብ ዘዴ የምንጠቀመው አትኩሮታችን አንድ የምንፈልገው ነገር ላይ ብቻ ስናደርግ ነው። ለምሳሌ አንድ አረፍተ ነገር ፣ ሀረግ ፣ ቃል ወይም ቁጥርን ቶሎ ብለን ለማግኘት ስናስብ ዝርዝር ነገሮችን ወደጐን በማድረግ አትኩሮታችነን በምንፈልገው ነገር ላይ በማድረግ ቶሎ ብለን ማንበብ ነው።
አንድን ፅሁፍ ምን ያህል ለኛ ጠቃሚ መሆኑን ለመገምገም ካሰብን የፅሁፉን የተወሰኑ ክፍሎቹን ብቻ እንቃኛ።
- የመጽሐፉን መቅድምና መግቢያ
- የምዕራፉን የመጀመሪያና የመጨረሻ አንቀፆችን
- የመጽሐፉን መደምደሚያ/ማጠቃለያ
- ሠንጠረዥ ፣ ግራፍ ፣ ካርታ ወ.ዘ.ተ
የግርፍ ንባብ ማለት የአንድን ፅሁፍ ዋና ነጥቦች ለማግኘት ፅሁፉን በፍጥነትና ዝርዝር ነገሮችን እየዘለሉ ማንበብ ነው። ለምሳሌ መፅሄት ፣ ጋዜጣ ፣ በራሪ ወረቀቶችን ስናነብ እንዲሁም በላይብረሪ ያለ ወይም ልንገዛው ያሰብነው መጽሐፍ ካለ ምን ያህል መጽሐፉ ለኛ ጠቃሚ መሆን ለማወቅ ስንል የምንጠቀመው የንባብ አይነት ነው። አንድን ፅሁፍ ወይም መጽሐፍ በዝርዝር ከማንበባችን በፊት አስቀድመን የሚከተሉትን ነገር እንመልከት:-
- ርዕሱን
- መቅድም
- መግቢያ
- ማጠቃለያ
- ሃይለቃሉን
- የተዘረዘሩ ነገሮችን
- ታላቅ ስራ የሰሩ ሰዎችን ማንነት
የዝግታ ንባብ ማለት የአንድን መጽሐፍ ወይም ጽሁፍ መልዕክት በጥልቅ ለመረዳት ቀስና ረጋ ብሎ እያንዳንዷን ቃል ፣ ሀረግ ፣ አረፍተነገርና አንቀፆችን ቀስና ረጋ ብሎ በደምብ ምበብ ነው።
አብዛሃኛዎቻችን በትምህርት ቤት የተሰጡን መጽሐፍት አንብበናል ግን ከመጽሐፎቹ በቂና ተፈላጊውን እውቀት ይዘን የወጣነው ጥቂቶች ነን። ለዚህም ትልቁ ምክኒያት ለምናነበው ነገር ትኩረት አለመስጠታችን ነው።
- እያሰመሩ ወይም ጠቃሚ ነጥቦችን በማስታዎሻ ደብተር ላይ እያወጡ ማንበብ
- እማናውቃቸውን ቃለት ለቅመን በማውጣት መሸምደድ
- በአትኩሮት ከማንበባችን በፊት የጽሁፉን ርዕስ ተመልክተን ምን ያህል ስለ ርዕሱ እንደምናውቅ ለመገምገም እራሳችነን የተወሰኑ ጥያቄዎችን እንጠይቅ። ለምሳሌ የአበባ አይነቶች የሚል ርዕስ ቢኖር ስንት የአበባ አይነቶች አሉ? እነማናቸው? የትና እንዴት ይበቅላሉ? ብለን እራሳችነን እንጠይቅ።
መጽሐፎችን ስናነብ ፣ የተለያዩ የመረጃ አውታሮችን ስንከታተል አዲስ ቃላት ከዚህ በፊት የማናውቃቸው ቃላት ሊገጥሙን እንደሚችል እሙን ነው። ታዲያ ይህ ችግር ለመቅረፍ ማለትም የምናነበውንና የምናዳምጠውን ነገር በትክክልና ሙሉ በሙሉ ለመረዳት አዲስ ቃላቶችን ማወቅ ይጠበቅብናል። ለዚህም መፍትሄው የመዝገበ ቃላት መጽሐፍ ከጐናችን እንዳይለየን ማድረግና ከዚህ በፊት የማናውቃቸውን ቃላት በማስታወሻ መዝግበን በመያዝ መሸምደድ ይጠበቅብናል።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|